print-logo2
A+ A-

ወንጌል ኢየሱስ | Gospel in Amharic

pdf

የወንጌል መልዕክት

–  እባክዎን የሚከተለውን ያንቡ።

ዘፍ. 1፡1 በመጀመሪያ እግዚሐብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
ሮሜ. 3፡23 ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚሐብሔር ክብር ጎድሎአቸዋል።
ዮሐ 8፡34 ኢየሱስ መለሰ፣ እንዲህ ሲል እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው።

እግዚሐብሔር እኛን ፈጥሮናል። ነገርግን አናወቀውም። በሠራነው ኃጢአት ከሱ ተለይቶናል። እግዚሐብሔር የሌለበት ሕይወታችን ትርጉምና ዓላማ የለውም። የኃጢአታችን ዋጋ መንፈሳዊና ስጋዊ ሞት ነው። መንፈሳዊ ሞት ማለት ከእግዚሐብሔር መለየት ማለት ነው። በሥጋ መሞት ማለት የአካል መበስበስ ማለት ነው። ከነኃጢአታችን ብንሞት ለዘላለሙ ከእግዚሐብሔር ጋር በመለየት ፍፃሜያችን በገሐነም መኖር ይሆናል። እንዴት ነው ራሳችንን ከኃጢአታችን ነጽተን ወደ እግዚሐብሔር የምንመለሰው? እኛ ራሳችንን ማዳን አንችልም። ምክንያቱም ኃጢአተኛ ሰው ራሱን ማዳን አይችልም። (በውሃ ዋና በመስመጥ ያለ ሰው ራሱን ማዳን እንደማይቻለው ሁሉ)። ሌሎችም እኛን ሊያድኑን አይችሉም። ምክንያቱን ሁላችንም ኃጢአት ሰርተናልና። (አንድ በመስመጥ ያለሰው ሌላውን ሊያድነው አይችልም፤ ምክንያቱም ሁለቱም ዕርዳታ ፈላጊዎች ስለሚሆኑ)። እኛን ከኃጢአታችን ለማዳን ኃጢአት የሌለበት ያስፈልገናል። (ከመስመጥ ያመለጠ)። ኃጢአት የሌለበት ሰው ነው ሊያድነን የሚችለው። ሁሉም በኃጢአት በወደቁበት ዓለም ኃጢአት ያልሰራ ሰው እንዴት ይገኛል?

ሮሜ 6፡23 የኃጢአት ደምወዝ ሞት ነውና፣ የእግዚሐብሔር የፀጋ ስጦት ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።
ዮሐ 3፡16 በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚሐብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን ሁሉ ወዶአልና።
ማቴ. 1፡23 “እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ይሉታል” ትርጓሜውም “እግዚሐብሔር ከእኛ ጋር ነው” የሚል ነው።
ዮሐ 8፡23 እሱም እንዲህ አላቸው “እናንተ ከታች ናችሁ፣ እኔ ከላይ ነኝ፣ እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፣ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም”። 
ማር 1፡11 “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፣ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።
ዮሐ 8፡36 እንግዲህ ልጁ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ።
ዮሐ 3፡3 እውነት እውነት እልሐለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በስተቀር የእግዚሐብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም አለው።
ዮሐ 1፡12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፣ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚሐብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።

የፈጠረንና በእጅጉ የሚወደን እግዚሐብሔር መፍትሄውን ሰጥቶናል። ወሰን ከሌለው ምህረቱ የተነሳ ለኃጢአታችን እንዲሞትልን የራሱን ልጅ ኢየሱስን ልኮልናል። ኢየሱስ ከዚህ ዓለም ስላልሆነ ኃጢአት የለበትም። በዓለም በነበረበትም ወቅት የዲያቢሎስን የኃጢአት ፈተና ተቋቁሟል። የሱ ሕይወት በሰማይ ያለውን እግዚሐብሔርን አስደስቷል። ኢየሱስ የኛን ኃጢአት በመረከብ ለኃጢአታችን ሲል በመስቀል ላይ ሞቶአል። እሱ የሕይወታችን አዳኝ ነው። (እየሱስ ሊያድነን የቻለው በመስጠም ላይ ስላልሆነ ነበር)። እየሱስ በመስቀል ላይ የሞተበት ዓላማ ለኃጢአታችን ዋጋ ለመክፈል ሲሆን ኃጢአታችንን ከኛ በማስወገድ ከእግዚሐብሔር ጋር ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነታችንን እንደገና ለማደስ ነው። በእግዚሐብሔር ኃይል አማካኝነት ከመንፈሳዊ ሞት በሕይወት ተርፈናል። (ከእግዚሐብሔር ከመለየት)። ይህ አዲሱ ግንኙነት ዳግም መወለድ ይባላል። ይህ ሂደት ወደተፈጠርንበት ዓላማና ሕይወት እንድንመለስ በማድረግ ለሕይወታችን ሐቀኛ ትርጉምና ዓላማ ያስገኝልናል።

ዮሐ 11፡25 ኢየሱስም “ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፣ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል” አላት።
ሮሜ 6፡9 ክርስቶስ ከሙታን ተነስቶ ወደፊት እንዳይሞት ሞትም ወደፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና።
የሐ.ሥ. 2፡24 እግዚሐብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፣ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።
ሮሜ 14፡9 ስለዚህ ነገር ሙታንንም ሕያዋንንም ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞቶአልና ሕያውም ሆኖአልና።
የሐ.ሥ. 1፡11 ደግሞም ፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።

ኢየሱስ ለኛ ኃጢአት ሲል በመሞት የከፈለው መስዋዕትነት እግዚሐብሔር በሰማይ እንደተቀበለው ምን ማስረጃ አለን? ማስረጃው እግዚሐብሔር ኢየሱስን ከሙታን በትንሳኤ ማስነሳቱ ነው። በትንሳኤው ኢየሱስ ሞትን አሸንፎታል። (በሌላ አነጋገር ሞት በእርሱ ላይ ስልጣን የለውም)። ስለዚህ አሁን ኢየሱስ ስለሚኖር እኛም እንኖራለን። በኛ ውስጥ ያለው ሕይወቱ ያኖረናል። ከሙታን በትንሳኤ ስለተነሳም ዛሬም ሕያው ነው።

ዮሐ 5፡24 “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፣ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም”።
ዮሐ 10፡9 በሩ እኔ ነኝ፣ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፣ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል።
ዮሐ 14፡6 ኢየሱስም “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ ከእኔ በቀር ወደአብ የሚመጣ የለም” አለው።
ዮሐ 8፡24 እንግዲህ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፣ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑም በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው።
የሐ.ሥ. 4፡12 መዳን በሌላ በማንመ የለም፣ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ሥም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።
ሮሜ 10፡13 “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና”።
ሮሜ 10፡11 መጽሐፍ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርምና” ይላልና።
ሮሜ 2፡11 እግዚሐብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።
ሮሜ 3፡22 እርሱም ለሚያምኑት ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚሐብሔር ፅድቅ ነው። ልዩነት የለምና።
ሮሜ 10፡9 ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚሐብሔር ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና።

ኃጢአታችን ተወግዶልን ይህን አዲሰ ሕይወት እንዴት ነው የምናገኘው? ይህ የሚሆነው ኢየሱስን እንደጌታ አዳኝ አድርገን ስንቀበለው ነው። ኃጢአታችንን ብንናዘዝና ኢየሱስ ይቅር እንዲለንና እንዲያድነን ብንለምነው ሊያደርገው ዝግጁ ነው። የእግዚሐብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ወደዓለም የመጣው ስለኃጢአታችን ለመሞት ነው። በዓለም ላይ ያለ ማንም ሰው በኢየሱስ ላይ እምነቱን ቢጥል ከእግዚሐብሔር ይቅርታን ያገኛል። ከኃጢአቱም (ከገሃነም) በመዳን አዲስ ሕይወት ከእግዚሐብሔር ይቀበላል። እግዚሐብሔር በሰዎች መካከል ልዩነት አያደርግም። የምንኖርበት አገር፣ የምንነጋገርበት ቋንቋ፣ ባለፀጋ ብንሆን ደሃ፣ ፆታችን ወንድ ቢሆን ሴት፣ ወጣት ብንሆን ሽማግሌ፣ ወይም ሌሎች ልዩነቶች ቢኖሩን በእግዚሐብሔር ዘንድ ለውጥ አያመጡም። በኢየሱስ የሚያምንና ጌትነቱን የሚቀበል ሁሉ ይድናል። ኢየሱስን ለመከተል ከወሰንክ ከዚህ በታች ያለውን ፀሎት መፀለይ ትችላለህ ፦

በሰማያት የምትኖር ልዑል እግዚሐብሔር ሆይ አንድያ ልጅህን ኢየሱስን ወደዚህ ዓለም በመላክ ስለኃጢአቴ ሞቶ ስላዳነኝና ከሰማይ የሆነ አዲስ ሕይወት እንድጎናፀፍ ስላደረከኝ አመሰግንሃለሁ። ስለክፉ ስራዬ ተፀፅቻለሁ። ኃጢአቴንም ይቅር እንድትለኝ እጠይቅሃለሁ። በኢየሱስ አምናለሁ፣ ኢየሱስንም እንደጌታዬና እንደግል አዳኜ አድርጌ ተቀብያለሁ። በሰጠኸኝ በዚህ አዲስ ሕይወት አንተን ደስ በሚያሰኝ ኑሮ እንድኖር አግዘኝ፣ ምራኝም። አሜን።

ከላይ የተጠቀሰውን ፀሎት ከፀለይክ በኋላ ወዴት ቤተክርስቲያ እንደምትሄድ እንዲያመለክትህ እግዚሐብሔርን ጠይቀው። ዘወትር ከእግዚሐብሔር ጋር በፀሎት ተገናኝ እግዚሐብሔርም ይናገርሃል። የእግዚሐብሔርን ድምፅ አዳምጥ። እግዚሐብሔርም ይመራሃል። እርሱ ይወድሃል፣ ይንከባከብሃልም። እምነትህን በእርሱ ላይ መጣል ትችላለህ። በእርሱ የሚታመኑትን አይተዋቸውም። እግዚሐብሔርም መልካም አምላክ ነው። ሊታመኑበት የተገባ ነው። ለሕይወትህ በእርሱ መመርኮዝ ትችላለህ። ፍላጎቶችህን በእርሱ ፊት አቅርብ፣ እርሱ ስላንተ ይጨነቃል ይባርክሃልም። እግዚሐብሔር እንዲህ ይላል “እኔ አንተን በፍፁም አልተውህም፣ አልጥልህም”። በኢየሱስ ስም ተባረክ።